ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ሕብረት ለምርጫ ታዛቢዎች ያለምንም ገደብ ወደ ጣቢያዎች ገብተው የምርጫውን ሂደት መታዘብ ችለዋል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ሕብረት ለምርጫ ታዛቢዎች ያለምንም ገደብ ወደ ጣቢያዎች ገብተው የምርጫውን ሂደት መታዘብ መቻላቸውን አስታወቀ።

ሕብረቱ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የእኩለ ቀን የትዝብት ሪፖርት ግኝቶች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የሕብረቱ የቦርድ ሰብሳቢ ሳህለሥላሴ አበበ፤  ሕብረቱ ለምርጫው ያሰማራቸውን ታዛቢዎች የእኩለ ቀን ሪፖርት በንባብ አሰምተዋል።

የቦርዱ ሰብሳቢው በመግለጫቸው፤ ሕብረቱ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 2ሺህ 258  ተቀማጭ እንዲሁም 891 ተንቀሳቃሽ በድምሩ 3ሺህ 149 ታዛቢዎች አሰማርቷል፡፡ 

ታዛቢዎቹ በ2ሺህ 258 የምርጫ ጣቢያዎች መሰማራታቸውን ጠቁመዋል።

በሕብረቱ ትዝብት መሰረት የድምፅ መስጫ ወረቀቶች፣ የቦርዱ ማህተም፣ የማይለቅ የጣት ቀለም፣ የድምፅ መስጫ ማሸጊያዎች፣ የመራጮች መዝገብ፣ የቦርዱ ድምጽ መስጫ ሳጥኖችን ጨምሮ የምርጫ ቁሳቁሶች መሉ በመሉ ተሟልቷል ብለዋል።

ከተቀበሏቸው ሪፖርቶች መካከል ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆኑ ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ላይ ታዛቢዎች ያለምንም ገደብ ወደ ጣቢያዎች ገብተው መታዘብ መቻላቸውን ጠቅሰዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም