የጊንጪ ከተማ ነዋሪዎች የኢትዮጵያን መጻኢ ዕድል የተሻለ ያደርጋል ብለው ላመኑበት ፓርቲ ድምፅ ሰጥተዋል - ኢዜአ አማርኛ
የጊንጪ ከተማ ነዋሪዎች የኢትዮጵያን መጻኢ ዕድል የተሻለ ያደርጋል ብለው ላመኑበት ፓርቲ ድምፅ ሰጥተዋል
አዲስ አበባ፤ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን መጻኢ ዕድል የተሻለ ያደርጋል ብለው ላመኑበት ፓርቲ ድምፅ መስጠታቸውን የጊንጪ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ በኦሮሚያ ክልል የጊንጪ ከተማ መራጮች በማለዳው በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን በዴሞክራሲያዊ መንገድ መስጠታቸውን ገልጸዋል።
ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ሀጂ ራህመቶ ሁሴን፤ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም በማለዳ ተነስተው ይበጀናል ለሚሉት ፓርቲ ድምፅ መስጠታቸውን ተናግረዋል።
ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ጽጌ ታደሰ፤ ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ ተጠቃሚነት ይበጃል ላሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምፅ መስጠታቸውን ገልጸዋል።
ምርጫ ለሀገር የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ በመሆኑ በማለዳ ተነስቼ ለሀገር ይጠቅማል ላልኩት ፓርቲ ድምፅ ሰጥቻለሁ ያሉት ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ ዘነበች ጉደታ ናቸው።
ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ሙሉ ቶሌራ በበኩላቸው፤ ከማለዳው 11 ሰዓት በመነሳት ለሀገር ይበጃል የምለውን ፓርቲ መርጫለሁ ብለዋል።