በድሬዳዋ የምርጫው ሒደት ግልጽና ሰላማዊ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በድሬዳዋ የምርጫው ሒደት ግልጽና ሰላማዊ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምርጫው ግልፅ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ተወካይና ተወዳዳሪ አቶ ዮናስ በትሩ ገለጹ።
በከተማ አስተዳደሩ ወረዳ 06 በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምጻቸውን የሰጡት አቶ ዮናስ በትሩ፤ የምርጫ ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊ እና ግልፅ በሆነ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ማስተዋላቸውን ገልጸዋል።
ጠንካራ እና ሉዓላዊ ሀገረ-መንግስት ለመገንባት በዲሞክራሲያዊ መንገድ በሕዝብ የተመረጠ ሕጋዊ መንግስት ሊኖር ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
ፍትሀዊ እና ታማኝ ምርጫ ማድረግ ለሀገሪቱ ቀጣይነት ቅድሚያ የሚሰጠው ዋና ጉዳይ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።