ለሀገር እድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት የሚሰራን ፓርቲ በመምረጥ የዜግነት ግዴታችንን ተወጥተናል-የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
ለሀገር እድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት የሚሰራን ፓርቲ በመምረጥ የዜግነት ግዴታችንን ተወጥተናል-የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
ሆሳዕና፤ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦ለሀገር እድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት የሚሰራን ፓርቲ በመምረጥ የዜግነት ግዴታችንን ተወጥተናል ሲሉ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ገለጹ።
ተማሪዎቹ ፥ነገ የሚረከቡትን ሀገር በተሻለ መልኩ ለሚገነባ ፓርቲ ድምጻቸውን በነፃነት መስጠታቸውን ገልጸዋል።
በዩኒቨርሲቲው የ4ኛ ዓመት የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪ እድላዊት አበበ የወሰደችውን ካርድ ተጠቅማ ለሀገር ይበጃል ላለችው ፓርቲ ድምጽ መስጠቷን ተናግራለች፡፡
ምርጫ በዴሞክራሲ የተገነባች ሀገርን ለመፍጠር እንደሚያግዝም ገልፃለች።
በዩኒቨርሲቲው የ4ኛ ዓመት የሰርጂካል ነርሲንግ ተማሪ ሀሰን አሊ በበኩሉ፥ በምርጫው ለሀገር ጠቃሚ ነው ለሚለው ፓርቲ ድምፅ ስለመስጠቱ ተናግሯል።
በዩኒቨርሲቲው የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል የ3ኛ ዓመት ተማሪዋ ረድኤት ኩቴና ዴሞክራሲያዊ መብቷን ተጠቅማ የተሻለች ሀገርን ለመገንባት የሚሰራ ፓርቲ ስለመምረጧ ተናግራለች።
ድምፅ በመስጠት ለሀገር እድገትና ለህዝብ ተጠቃሚነት የሚሰራን ፓርቲ በመምረጥ የዜግነት ግዴታቸውን እንደተወጡ የተናገሩት ደግሞ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ዳንኤል ሀንዲኖ (ዶ/ር) ናቸው።