ምርጫ የዜጎች የዴሞክራሲ ተሳትፎ የሚገለጽበት በመሆኑ ድምጻችንን ለሀገር ይጠቅማል ብለን ላመንበት ፓርቲ ሰጥተናል - ኢዜአ አማርኛ
ምርጫ የዜጎች የዴሞክራሲ ተሳትፎ የሚገለጽበት በመሆኑ ድምጻችንን ለሀገር ይጠቅማል ብለን ላመንበት ፓርቲ ሰጥተናል
ሮቤ ፤ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦ምርጫ የዜጎች የዴሞክራሲ ተሳትፎ የሚገለጽበት በመሆኑ ድምጻችንን ለሀገር ይጠቅማል ብለን ላመንበት ፓርቲ ሰጥተናል ሲሉ በባሌ ሮቤና ጎባ ወረዳ የምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፃቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ገለጹ።
የባሌ ሮቤና ጎባ ወረዳ መራጮች በምርጫው ለሀገር ይበጃል ብለው ላመኑት ፓርቲ ድምጻቸውን በነፃነት መስጠታቸውን ገልጸዋል።
አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል አቶ አብዱራህማን ከድር በማለዳው ካርድ ባወጣንበት የምርጫ ጣቢያ በመገኘት ዴሞክራሲያዊ መብታችንን በመጠቀም ለሀገር ይበጃል ያልነውን ፓርቲ መርጠናል ብለዋል።
በምርጫ ጣቢያው ቅድሚያ ተሰጥቶኝ በድምፄ ይወክለኛል ያልኩትን ፓርቲ በነጻነት መርጫለሁ ብለዋል።
በምርጫ ጣቢያው በማለዳ በመገኘት ይበጀኛል ለምለው ፓርቲ ድምፅ ሰጥቻለሁ ያሉት ደግሞ በአሊ ቢራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምርጫ ጣቢያ ድምጻቸውን የሰጡት ወይዘሮ አረቤ ባቲ ናቸው።
አካል ጉዳተኛው ሐጂ ሁሴን በበኩላቸው ምርጫ የዜጎች የዴሞክራሲ ተሳትፎ የሚገለጽበት መሆኑን በመረዳት አካል ጉዳተኝነት ሳይበግረኝ በማለዳ ወጥቼ ድምፄን በቀጣይ ለሚመራኝ አካል ሰጥቻለሁ ብለዋል።
በባሌ ዞን ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ ህዝቡ በነቂስ በመውጣት ድምጹን በመስጠት ላይ ይገኛል።