ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018(ኢዜአ)፦ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ በመርሃ ግብሩ መሰረት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገለጹ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እየተካሄደ የሚገኘውን ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም፤ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደት ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ልዩ ልዩ የቅደመ ምርጫ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል።
ምርጫውን ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ገለልተኛ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውንም ተናግረዋል።
ቦርዱ እነዚህን የቅደመ ምርጫ ዝግጅቶች አጠናቆ ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።
መራጩ ህዝብም ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በየምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት በነጻነት ድምፁን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።