ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ድምፃቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ፤ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በአራዳ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 6 በመገኘት ድምፃቸው ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በዛሬው እለት ድምፅ እየተሰጠ ነው።

በዚህም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 6 በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

በምርጫ ጣቢያው ካርድ የወሰዱ ዜጎችም ከማለዳው ጀምሮ ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም