በሰባት የኢትዮጵያ ምርጫዎች ድምጽ የሰጡት የዕድሜ ባለጸጋዋ እናት - ኢዜአ አማርኛ
በሰባት የኢትዮጵያ ምርጫዎች ድምጽ የሰጡት የዕድሜ ባለጸጋዋ እናት
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018(ኢዜአ)፦ በሰባት የኢትዮጵያ ምርጫዎች ድምጽ የሰጡት የዕድሜ ባለጸጋዋ እናት ምንትዋብ አዘነልኝ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጽ ሰጥተዋል።
የ90 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋዋ ምንትዋብ አዘነልኝ በባሕር ዳር ምርጫ ክልል ጣና 02 ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምጽ ሰጥተዋል።
ከዚህ በፊት በተካሄዱ ስድስት ምርጫዎች ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ አስታውሰው ዛሬም ድምጽ ሰጥቻለሁ ብለዋል።