ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በነቀምቴ ከተማ ድምፅ ሰጡ - ኢዜአ አማርኛ
ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በነቀምቴ ከተማ ድምፅ ሰጡ
ነቀምቴ ፤ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በነቀምቴ ከተማ ድምፅ ሰጡ።
ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ድምፅ ከሰጡ በኋላ በሰጡት አስተያየት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሕዝብ ድምፅ ትልቅ ዋጋ እንዳለው በተግባር የሚታይበት ነው ብለዋል።
ምርጫ በየአምስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ድምፅ በመስጠት ሥልጣን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ብቻ እንዲሸጋገር ማድረጊያ አንዱ መንገድ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሕዝቡ የሚፈልገውን ፓርቲ በመምረጥ ኃላፊነቱን ሲወጣ ማየት ትልቅ ትርጉም እንዳለውም አስረድተዋል።