በማለዳ ተነስተን ድምጻችንን በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ተጠቅመናል - በጅማ ዞን የሸቤ ከተማ ነዋሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
በማለዳ ተነስተን ድምጻችንን በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ተጠቅመናል - በጅማ ዞን የሸቤ ከተማ ነዋሪዎች
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018(ኢዜአ)፦ በማለዳ ተነስተን ድምጻችንን በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ተጠቅመናል ሲሉ በጅማ ዞን የሸቤ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እየተካሄደ በሚገኘው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በጅማ ዞን የሸቤ ሶምቦ ወረዳ የሸቤ ከተማ መራጮች በማለዳ ተነስተው በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
የሸቤ ከተማ ነዋሪው አቶ መሐመድ አደም ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ በሰጡት አስተያየት፤ ሂደቱ እጅግ የተቀላጠፈ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም በማለዳ ተነስተው ለሀገር ዕድገት ይበጃል ላሉት አካል ድምፅ መስጠታቸውን ተናግረዋል።
ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ካሳሁን መኩሪያ በበኩላቸው ምርጫ ለሀገር ዴሞክራሲ መጎልበት ወሳኝ በመሆኑ በማለዳ ተነስተው ድምፅ መስጠታቸውን ገልጸዋል።
ሁሉም ዜጋ ድምጹን በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብቱን እንዲያረጋግጥም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሀገር ጉዳይ ይመለከተኛል በሚል እሳቤ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ድምጹን መስጠቱን የገለጸው ደግሞ ወጣት አብዲ አወል ነው።