በደሴ ከተማ መራጮች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በደሴ ከተማ መራጮች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው
ደሴ፤ግንቦት 24/2018(ኢዜአ)፦በደሴ ከተማ ኢትዮጵያ ትመርጣለች በሚል መርህ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ መስጠት ተጀምሯል።
ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ መራጮች ተሰልፈው ወረፋቸውን በመጠበቅ ድምፃቸውን በነፃነት መስጠት ጀምረዋል።
የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው አሰራር መሰረት ከማለዳ እስከ ምሽት የሚቀጥል ይሆናል።