ቀጥታ፡

በጋምቤላ ከተማ መራጮች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው

ጋምቤላ፤ግንቦት 24/2018(ኢዜአ)፦በጋምቤላ ከተማ መራጮች በማለዳ ወጥተው ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።

የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) በጋምቤላ ከተማ አስተዳድር ምርጫ ክልል በ01 ቀበሌ በመካነእየሱስ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።


 

በከተማው የድምፅ አሰጣጡ ሂደት የምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ መራጮች ተሰልፈው ወረፋቸውን በመጠበቅ ድምፃቸውን መስጠት ጀምረዋል።

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው አሰራር መሰረት ከማለዳ እስከ ምሽት 12 ሰዓት የሚቀጥል ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም