ቀጥታ፡

በሻሸመኔ ከተማ መራጮች ድምፅ እየሰጡ ነው

ሻሸመኔ፤ ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦ በሻሸመኔ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እየተካሄደ ይገኛል።

በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ከሌሊት ጀምሮ ሰልፎችን በመያዝ ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው አሰራር መሰረት የምርጫ ታዛቢዎችና አስፈፃሚዎች በተገኙበት ምስጢራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ እየተካሄደም ይገኛል።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 871 መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ፤ 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እንዲሁም 80 የግል እጩዎች የሚወዳደሩ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም