ቀጥታ፡

በጋምቤላ ክልል ጎግ ወረዳ ምርጫ ክልል ነገ ለሚካሄደው ምርጫ የተደረገው ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል

ጎግ ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በአኝዋሃ ዞን ጎግ ወረዳ ምርጫ ክልል በነገው ዕለት ከማለዳ ጀምሮ ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ  የተሟላ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ። 

የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ አቶ ንብረት ሰውየው ለኢዜአ አንደገለፁት በምርጫ ክልሉ በሚገኙ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በነገው እለት ለሚካሄደው ምርጫ የቁሳቁስ ስርጭት በተሟላ ሁኔታ መደረጉን ነው የገለፁት። ‎


 

የምርጫ ታዛቢዎችም በየምርጫ ጣቢያው በሰዓቱ  በመገኘት ሂደቱን ለመታዘብ ዝግጁ መሆናቸውንም አብራርተዋል። ‎ 

በ‎ወረዳው የምርጫ ክልል 19 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም