ቀጥታ፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር እና ኡሁሩ ኬንያታ በምርጫ ታዛቢ ቡድኖች ዝግጅት ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ፣ ከአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ከሆኑት ከኡሁሩ ኬንያታ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ ስለ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅድመ-ዝግጅቶች እና ታዛቢ ቡድኖች ግልጽና ዲሞክራሲያዊ ሂደቶችን በመደገፍ ረገድ ያላቸው ሚና ላይ ያተኮረ ነው።

በተጨማሪም በአፍሪካ ህብረት የተለያዩ ተልዕኮዎች ዙሪያም ሀሳቦችን መለዋወጣቸውን የህብረቱ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም