አትሌት ሰለሞን ባረጋ የታላቁ ማንችስተር የጎዳና ሩጫ ውድድርን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
አትሌት ሰለሞን ባረጋ የታላቁ ማንችስተር የጎዳና ሩጫ ውድድርን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦ አትሌት ሰለሞን ባረጋ ዛሬ በተካሄደው የታላቁ ማንችስተር የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድር ድል ቀንቶታል።
አትሌት ሰለሞን ውድድሩን ለማጠናቀቅ 27 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ ፈጅቶበታል።
አትሌቱ ባለፈው ዓመት ውድድሩን ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
ኡራጓዊው አትሌት ሳንቲያጎ ካትሮፌ ሁለተኛ እና ዩጋንዳዊው ኦስካር ቼሊሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ኦማር መሐመድ 28 ደቂቃ ከ27 ሴኮንድ ስምንተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በሴቶች የስሎቬኒያዋ አትሌት ክላራ ሉካን 30 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ አንደኛ ወጥታለች።
አሜሪካዊቷ ዌኒ ኬላቲ ሁለተኛ ስትወጣ ኤሚ-ኢሎይስ ኒል (ታላቋ ብሪታኒያ) ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች።
እ.አ.አ በ2003 የተጀመረው የታላቋ ማንችስተር የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ በዓለም አትሌቲክስ የወርቅ ደረጃ የተሰጠው ታዋቂ የጎዳና ላይ ውድድር ነው።