ቀጥታ፡

በሲዳማ ክልል የቱላ እና ጉጉማ የምርጫ ክልሎች ለነገው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል

ውጅግራ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የቱላ እና ጉጉማ ምርጫ ክልሎች ነገ ከማለዳው ጀምሮ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገለጹ።

የቱላ ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ ምንተስኖት ስምኦን እንደገለጹት በምርጫ ክልሉ የሚገኙ 156 የምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ ስርጭት ተደርጓል።

ጣቢያዎቹ በነገው ዕለት ከማለዳው ጀምሮ ለሚካሔደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በምርጫ ክልሎቹ ከቦርዱ የተሰጡ ተግባራትን የሚያሳልጡ አስፈጻሚዎች ስምሪት ወስደው ስራ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የጉጉማ ምርጫ ክልል አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ደንግሶ በበኩላቸው በምርጫ ክልሉ በሚገኙ 78 የምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ ስርጭት፣ የድንኳን ተከላና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ተጠናቀው የድምጽ አሰጣጡን እየተጠባበቁ ይገኛሉ ብለዋል።

በምርጫ ጣቢያዎቹ አስፈጻሚዎች ስምሪት ወስደው በስራ ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም