ቀጥታ፡

በደሴ ከተማ ምርጫ ክልል ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ለነገው ምርጫ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል

ደሴ ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦ በደሴ ከተማ ምርጫ ክልል ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ለነገው ምርጫ ዝግጁ መሆናቸውን የምርጫ ጣቢያ አስተባባሪዎች ገለጹ።

በደሴ ከተማ ምርጫ ክልል የአገር ግዛት ምርጫ ጣቢያ "ሀ" እና "ለ" አስተባባሪ አቶ አራጋው ተስፉ፣ በነገው እለት ለሚካሄደው ምርጫ የምርጫ ጣቢያዎቹ የተሟላ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የሆጤ ምርጫ ጣቢያ "ለ" አስተባባሪ አቶ ማስረሻ ጥላሁን እና ሌላኛዋ አስተባባሪ ወይዘሮ የምስራች መኮንን፤ ለምርጫው ዝግጅቱ ተሟልቶ ነገን እየጠበቅን እንገኛለን ብለዋል።

በደሴ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ 110 የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ ተሟልቶ ለነገው ምርጫ ዝግጁ መሆናቸው ታውቋል።

በመሆኑም መራጮች የምርጫ ካርዳቸውን በመያዝ ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ ድምፃቸውን ለመስጠት ተዘጋጅተው እንዲመጡ አስተባባሪዎቹ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም