ቀጥታ፡

በደንዲ ሁለት የምርጫ ክልል ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶች ተሰራጭተዋል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦በደንዲ ሁለት የምርጫ ክልል ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶች መሰራጨታቸውን የምርጫ ክልሉ ኃላፊ አቶ ኢቲቻ ለታ ገለጹ።

ለምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ የሆኑት ግብዓቶች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች፣ የመራጮች መዝገብ ፣ የድምጽ መስጫ ኮሮጆና የተለያዩ ቁሳቁሶች መሰራጨታቸውን ገልፀዋል።

የቁሳቁስ ስርጭቱ በጥንቃቄና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እየተከናወነ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ተደራሽ መደረጉን ጠቁመዋል። 

የምርጫ ቁሳቁሶቹ በአግባቡ በምርጫ ጣቢያዎች መድረሳቸውን ተናግረዋል። 

በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ በርካታ መራጮች በተመዘገቡበት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድምጽ ይሰጣል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም