ቀጥታ፡

የጊንጪ ከተማ ነዋሪዎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም ተዘጋጅተዋል  

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦ነገ ማለዳ በምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን በምዕራብ ሸዋ ዞን የጊንጪ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። 

አስተያየታቸውን የሰጡት የከተማዋ ነዋሪዎች እንዳሉት፤ ይበጀናል ለሚሉት ድምጽ ለመስጠት በጉጉት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም መሠረት ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀምና የሚፈልጉትን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።

ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከልም አቶ ቤለማ አብዶ እንዳሉት በማለዳ ተነስተው ድምጻቸውን ለሚፈልጉት ፓርቲ ለመስጠት ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡  

ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ገላና ዲንቃ በበኩላቸው ምርጫ የዜጎች የዴሞክራሲ ተሳትፎ መሆኑን ገልጸው ነገ በማለዳ ተነስተው ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ 

በምርጫው ለሀገር ይጠቅማል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

ነገ በማለዳው ካርድ ባወጣንበት የምርጫ ጣቢያ ተገኝተን ለመምረጥ ተዘጋጅተናል ያሉት ደግሞ አቶ ምትኩ ቤኩማ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

ቦርዱ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውንም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም