ቀጥታ፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል

ደብረ ማርቆስ ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦የወሰዱት ካርድ ዋጋ እንዲኖረው ድምጽ ለመስጠት ነገ በማለዳ በአካባቢያቸው በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

ነዋሪዎቹ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት እንደገለፁት፤ የወሰዱት ካርድ ዋጋ እንዲኖረው ድምጽ ለመስጠት ነገ በማለዳ በአካባቢያቸው በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ለመገኘት ተዘጋጅተዋል።

በከተማው የቀበሌ 19 ነዋሪ የሆኑት አቶ ያለው አወቀ፤ ለሀገር ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ነገ በማለዳ ወደ ምርጫ ጣቢያ ለመሄድ እንደተዘጋጁ ገልጸዋል።

ለዚህም ቀደም ሲል የምርጫ ካርድ በመውሰድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያደረጉት ክርክርና የምርጫ ቅስቀሳ ሲከታተሉ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

ነገ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ካርዴን ተጠቅሜ ለምፈልገው ፓርቲ ድምጼን ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ ያሉት ደግሞ የዚሁ ቀበሌ ነዋሪው አቶ አያልነህ ሰዋለም ናቸው።

በከተማው የቀበሌ 07 ነዋሪው አቶ እድሜአለም መሰረት በበኩላቸው፤ የወሰዱት ካርድ ዋጋ እንዲኖረው ማልደው በመነሳት ለመምረጥ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለሀገር ዕድገት ይበጃል ለሚሉት ፓርቲ ድምፃቸውን ለመስጠት እንዳሰቡም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም