ለነገው ምርጫ ከማለዳው ጀምሮ ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል -የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
ለነገው ምርጫ ከማለዳው ጀምሮ ድምጻችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል -የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች
ወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦ለነገው ምርጫ ከማለዳው ጀምሮ ድምፃችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል ሲሉ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ መስጠት ስነ ስርአት በነገው እለት ከማለዳው 12 ሰአት ጀምሮ የሚካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
ለዚህም በየምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶች ደርሰው ለድምጽ አሰጣጡ የተሟላ ዝግጅት ተደርጓል።
በዚሁ መሰረት ከማለዳው ጀምሮ በካርዳቸው ድምፅ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ የምርጫ ካርዳ ለማውጣት የነበራቸውን ተሳትፎ ድምፅ በመስጠት ለመድገም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።