ቀጥታ፡

በጭፍራ ምርጫ ክልል ስር የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል

ጭፍራ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦ በአፋር የጭፍራ ምርጫ ክልል ስር የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ አቶ  አሊ ከማል ገለጹ።

የጭፍራ ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ አሊ ከማል እንደገለፁት፤በጭፍራ ምርጫ ክልል ስር የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በወቅቱ አሟልተውና የአስፈጻሚዎችን አቅም ገንብተው ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው፣ መላው የመራጭ ማህበረሰብ ያለምንም እንግልት የዜግነት መብቱን እንዲጠቀም ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።

በምርጫ ክልሉ ስር በሚገኙት 113 የምርጫ ጣቢያዎች ለነገው ምርጫ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።

በጣቢያዎቹ የምርጫ ቁሳቁሶች መሰራጨታቸውን ገልፀው ታዛቢዎችና አስፈጻሚዎች በተሳካ ሁኔታ መድረሳቸውን ጠቁመዋል።

በዚህም መሠረት በነገው ዕለት ለሚካሄደው  ምርጫ ዝግጅቶች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸውን አስተባባሪው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም