ለምርጫው አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀናል - የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች - ኢዜአ አማርኛ
ለምርጫው አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀናል - የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች
ሐረር ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦ ለምርጫው አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀናል ሲሉ በሐረሪ ክልል የሚገኙ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ተናገሩ።
ነገ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን በሐረሪ ክልል የምርጫ ጣቢያዎች አስፈጻሚዎች ተናግረዋል።
በክልሉ ሁንደኔ፣ ጀጎል ዙሪያና ጀጎል ልዩ የምርጫ ክልል ስር የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አስፈጻሚዎች በሰጡት አስተያየት፤ የድምፅ መስጫ ሳጥኖችንና ወረቀቶችን ጨምሮ ሌሎች ለድምጽ መስጫ ሂደቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ ተሟልተው መቅረባቸውን ተናግረዋል።
የሁንደኔ እና የጀጎል ልዩ ምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ከሆኑት መካከል አብረሃም አየለ እና ቤተልሄም አረጋ እንደተናገሩት፤ በምርጫ ጣቢያዎቹ መራጮች ድምፃቸውን መስጠት የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።
በምርጫ ጣቢያዎቹ ለድምፅ መስጫ የሚያገለግሉ ቁሶች መሟላታቸውንና የድምጽ መስጫ ቦታዎችን ምቹ የማድረግ ስራም መከናወኑን ተናግረዋል።
መራጩ ሕዝብ በነገው ዕለት ከንጋት ጀምሮ በየምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት ሕገ መንግሥታዊ መብቱን እንዲጠቀምና ድምፁን እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
በሐረሪ ክልል ሶስት የምርጫ ክልሎች እና 296 የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።