ቀጥታ፡

በወሰድነው የምርጫ ካርድ ለሀገር ይበጃል የምንለውን ለመምረጥ የነገውን ዕለት በጉጉት እየጠበቅን ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23/2018(ኢዜአ)፦ በወሰዱት የምርጫ ካርድ ለሀገር ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የነገውን ዕለት በጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸውን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የኤጄሬ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውን አስታውቋል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው የኤጄሬ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ባስተላለፏቸው መልዕክቶች በቂ ግንዛቤ መጨበጣቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሠረት ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በአግባቡ ለመጠቀም ነገ ማልደው በመነሳት የሚፈልጉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

አስተያየታቸውን ከሰጡት የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ደረጀ ኃይሉ፤ የምርጫ ካርዳቸውን ቀድመው መውሰዳቸውን ጠቅሰው የነገውን ዕለት በጉጉት እየተጠባበቁ መሆኑን አስታውቀዋል።

አቶ ታፈሰ ተሬሳ በበኩላቸው ምርጫ የዜጎች የዴሞክራሲ ተሳትፎ መሆኑን ገልፀው ነገ በጥዋት ወጥተው ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

በማለዳ ተነስተው ድምጻቸውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን የገለጹት ሌላኛዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ሙሉ ፉፋ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም