ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የካራቴ ሻምፒዮና አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አገኘች

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የካራቴ ሻምፒዮና ከግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ይገኛል።

በሻምፒዮና ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ካራቴ ብሔራዊ ቡድን እስከ አሁን ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን አግኝቷል።

ብሔራዊ ቡድኑ በወንዶች ከ75 ኪሎ ግራም በታች እና ከ53 ኪሎ ግራም በታች፣ እንዲሁም በሴቶች ካታ እና በቡድን የካራቴ ኩሚቴ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችሏል።

በተጨማሪም በወንዶች ከ67 ኪሎ ግራም በታች እና በቡድን ካታ ውድድር ሁለት የብር ሜዳሊያዎች ተገኝተዋል።

በወንዶች ካታ፣ ከ60 ኪሎ ግራም በታች እና ከ84 ኪሎ ግራም በታች ሶስት የነሐስ ሜዳሊያዎች የተመዘገበባቸው ሌሎች ዘርፎች ናቸው።

የምስራቅ አፍሪካ የካራቴ ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን አምስት አገራት መሳተፋቸውን የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2025 በአዲስ አበባ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ የካራቴ ሻምፒዮና አጠቃላይ አሸናፊ እንደነበረች የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም