ቀጥታ፡

በደብረ ማርቆስ ከተማ የምርጫ ጣቢያዎች ለድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል

ደብረ ማርቆስ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦ በደብረ ማርቆስ ከተማ በምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶች ተሰራጭተው ለድምጽ አሰጣጥ ዝግጁ መሆናቸውን የከተማዋ ምርጫ ክልል አስተባባሪ ገልጸዋል።

በምርጫ ክልሉ ስር በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በሙሉ የምርጫ ቁሳቁስ መድረሱን የደብረ ማርቆስ ከተማ ምርጫ ክልል አስተባባሪ አንሙት መንግሥት ተናግረዋል።

በነገው እለትም ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ለሚከናወነው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት የምርጫ ጣቢያዎቹ ዝግጁ መሆናቸውን  አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም