በአዲስ ዓለም /ኤጄሬ የምርጫ ክልል የድምጽ መስጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ ዓለም /ኤጄሬ የምርጫ ክልል የድምጽ መስጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ ዓለም /ኤጄሬ የምርጫ ክልል የድምጽ መስጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ነው።
የምርጫ ጣቢያው ኃላፊ ጉርሜሳ መደቅሳ የምርጫ ቁሳቁስ ለምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ እንደሚገኝ ለኢዜአ ተናግረዋል።
ለምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ የሆኑት ግብዓቶች ማለትም የድምጽ መስጫ ወረቀቶች፣ የመራጮች መዝገብ፣ የድምጽ መስጫ ኮሮጆን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ የሚባሉ ቁሳቁሶች እየተሰራጩ ነው ብለዋል።
የቁሳቁስ ስርጭቱ በጥንቃቄና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እየተከናወነ እና ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ተደራሽ እየተደረገ ይገኛል ሲሉም ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ በርካታ መራጮች በተመዘገቡበት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድምጽ ይሰጣል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ሰኞ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ለመስጠት 54 ሚሊየን 57ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውን አስታውቋል።