በሰቃ ጮቆርሳ ሁለት የምርጫ ክልል ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አሰፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል - ኢዜአ አማርኛ
በሰቃ ጮቆርሳ ሁለት የምርጫ ክልል ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አሰፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 23/2018(ኢዜአ)፦ በሰቃ ጮቆርሳ ሁለት የምርጫ ክልል ነገ ለሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የምርጫ ክልሉ ሃላፊ ብሩክ ታሪክ ገለጹ።
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መርሃ ግብር መሰረት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቀ ሲሆን፣ ዜጎችም የድምፅ መስጫውን እለት በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
የሰቃ ጮቆርሳ ሁለት የምርጫ ክልል ሃላፊ ብሩክ ታሪክ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በምርጫ ክልሉ 97 የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ።
በስሩ ለሚገኙ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ሂደቱን በስኬት መወጣት የሚያስችሉ ሎጂስቲክስን ጨምሮ አስፈላጊ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።
ለምርጫው ሂደት ወሳኝ የሆኑት የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች የምርጫ ጣቢያ ድረስ በወቅቱና በጥንቃቄ መሰራጨታቸውን አረጋግጠዋል።
የድምጽ መስጫ ቦታዎች አካል ጉዳተኞችንና አቅመ ደካሞችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ዝግጁ መደረጋቸውንም አስታውቀዋል።
መራጩ ህዝብም በምርጫው ቀን በማለዳ በድምጽ መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ ድምጹን እንዲሰጥ መልዕክት አስተላልፈዋል።