በደሴ ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በደሴ ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ ነው
ደሴ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦በደሴ ከተማ አስተዳደር በነገው እለት ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ ነው።
በዚሁ መሰረትም በከተማዋ ለሚገኙ 110 የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ መስጫ ሳጥኖች፣ የመራጮች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እና ሌሎችም ቁሳቁሶች እየደረሱ ነው።
የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ከማከናወን ባለፈ ምርጫ ለማከናወን የሚያስችል ምቹ ሁኔታ የመፍጠሩ ሂደት በተሳካ ሁኔታ እየተተገበረ መሆኑም ተመላክቷል።
የከተማው ነዋሪዎችም በካርዳቸው በነገው እለት ድምፃቸውን ለመስጠት እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።