ቀጥታ፡

በድሬዳዋ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ነው

ድሬደዋ፤ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ነው።

በነገው ዕለት ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለድምፅ አሰጣጡ የተሟላ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረትም በአስተዳደሩ የምርጫ ቁሳቁሶች ከትናንት ጀምሮ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዚያድ ያሲን መሐመድ፤ የምርጫ ቁሳቁሶች በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት ሙሉ በሙሉ በየምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶቹ ተደራሽ ይሆናሉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም