በካርዳችን ድምጽ በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም ተዘጋጅተናል -የጭፍራ ከተማ ነዋሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
በካርዳችን ድምጽ በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም ተዘጋጅተናል -የጭፍራ ከተማ ነዋሪዎች
ጭፍራ፤ ግንቦት 23/2018 (ኢዜአ)፦ በካርዳችን ድምጽ በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም ተዘጋጅተናል ሲሉ በአፋር ክልል የጭፍራ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ በነገው ዕለት በሚካሄደው ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በካርዳቸው ድምጽ በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል።
ከከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ አህመድ ሙስጠፋ በነገው ዕለት በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
የከተማዋ ነዋሪ ወጣት መሐመድ ሃመድ በበኩሉ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፁን በመስጠት ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለመጠቀም መዘጋጀቱን ተናግሯል።
በዚህም የምርጫውን ቀን እየጠበቀ መቆየቱን እና በነገው ዕለት በማለዳ ወደ ምርጫ ጣቢያ እንደሚያቀናም ገልጿል።
በነገው ዕለት በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በመገኘት ይበጀናል ለሚሉት ፓርቲ ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን የገለፁት ደግሞ አቶ መሐመድ ማህሙድና አሚን መሐመድ ናቸው።
በድምፃቸው የወደፊቱን የሀገር መሪ ለመምረጥ ዝግጁ ሆነው የምርጫውን ቀን እየተጠባበቁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ወይዘሮ ሰአዳ ሰኢድ በበኩላቸው፤ በወሰዱት ካርድ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም የሚበጃቸውን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።