ሲዳማ ቡና የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት የተቃረበበትን ወሳኝ ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት የተቃረበበትን ወሳኝ ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 22/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን በ22ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በሊጉ 17ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሲዳማ ቡና በ61 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።
ሲዳማ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት የተቃረበበትን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
ቡድኑ በ35ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡናን ካሸነፈ የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል።
ከቀናት በፊት ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ያለፈው ሲዳማ ቡና ሁለት ዋንጫ የማንሳት ህልሙን ማስቀጠል ችሏል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ39 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።
ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው አዳማ ከተማ የወራጅነት ስጋት አንዣቦበታል።