ሊቨርፑል አሰልጣኝ አርን ስሎትን አሰናበተ - ኢዜአ አማርኛ
ሊቨርፑል አሰልጣኝ አርን ስሎትን አሰናበተ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 22/2018 (ኢዜአ)፦ ሊቨርፑል የክለቡን ዋና አሰልጣኝ አርን ስሎት (Arne Slot) ማሰናበቱን አስታወቀ።
ደካማ እና አጥጋቢ ያልሆነ የ2025-26 የውድድር ዓመት ካሳለፉ በኋላ በከፍተኛ ጫና ውስጥ የነበሩት ኔዘርላንዳዊው የ47 ዓመት አሰልጣኝ፣ የክለቡ አመራሮች ጋር ባደረጉት የውድድር ዓመት ግምገማ ላይ ከሊቨርፑል ጋር ያላቸው ቆይታ ማክተሙ ታውቋል።
እ.አ.አ በ2024 የሊቨርፑል አሰልጣኝነትን ከየርገን ክሎፕ በመረከብ ስራ የጀመሩት አሰልጣኙ ቡድኑን በመጀመሪያ ዓመታቸው ለሊጉ ዋንጫ ማብቃተቸው ይታወሳል።
ሊቨርፑል በ60 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ቢያልፍም ስሎትን ከስንብት አልታደጋቸውም።
አሰልጣኙ እስከ 2027 (እ.አ.አ) የሚያቆይ ውል ነበራቸው።
አርን ስሎት አንፊልድን መልቀቃቸውን ተከትሎ፣ የቀድሞው የቦርንማውዝ አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ ቀጣዩ የሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ ለመሆን ቀዳሚው እጩ ሆነው ቀርበዋል።