በሰቆጣ ምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በሰቆጣ ምርጫ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ ነው
ሰቆጣ ፤ ግንቦት 22/2018 (ኢዜአ)፦ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ምርጫ ክልል ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚያገለግሉ የምርጫ ቁሳቁሶች ስርጭት እየተከናወነ ነው።
ለጠቅላላ ምርጫው እየተካሄደ ያለው የቁሳቁስ ስርጭትም ቀድሞ በተያዘለት መርሃ ግብር በተቀናጀ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።
በዚህም ምርጫው በሚከናወንባቸው ሁሉም አካባቢዎች የምርጫ ቁሳቁስ ከምርጫ ክልሎች በስሮቻቸው ወደ ሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ስርጭት እየተከናወነ መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ።
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰቆጣ ምርጫ ክልልም በውስጡ ወደሚገኙ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ እንደሚገኝም ተመልክቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።