ቀጥታ፡

የምርጫ ካርድ በመውሰድ ያሳየነውን የነቃ ተሳትፎ ድምፅ በመስጠት ለመድገም ተዘጋጅተናል

ጋምቤላ ፤ ግንቦት 22/2018 (ኢዜአ)፦ በምርጫው ሂደት ካርድ በመውሰድ ያሳየነውን የነቃ ተሳትፎ ድምፅ በመስጠት ለመድገም ተዘጋጅተናል ሲሉ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚፎካከሩበትና 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች የተመዘገቡበት የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል።

ለዚህም በየአካባቢው የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ የሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶች እየተሰራጩ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ድምፃቸውን ለመስጠት ያላቸውን ዝግጁነት በተመለከተ የኢዜአ ሪፖርተር ተዘዋውሮ አነጋግሯቸዋል።

ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ ታየ ሻፍቱ፣ አቶ ኡሞድ ኡሞድ እና አቶ ወንድሙ ለማ፤ በምርጫው ሂደት ካርድ በመውሰድ ያሳየነውን የነቃ ተሳትፎ ድምፅ በመስጠት ለመድገም ተዘጋጅተናል ሲሉ ገልጸዋል።

በእለቱ ማልደው በመውጣት ለሀገር ልማትና እድገት ይበጃል የሚሉትን የፖለቲካ ፓርቲ በመምረጥ ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በምርጫው ሂደት ካርድ በመውሰድ ያሳየነውን የነቃ ተሳትፎ ድምፅ በመስጠት ለመድገም ተዘጋጅተናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም