በባሕርዳር ከተማ ምርጫ ክልል በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በባሕርዳር ከተማ ምርጫ ክልል በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው
ባህርዳር፤ ግንቦት 22/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ባሕርዳር ከተማ ምርጫ ክልል በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው።
የፊታችን ሰኞ የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚፎካከሩበትና 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች የተመዘገቡበት ታሪካዊ የምርጫ ሂደት ነው።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተሟላ ዝግጅት በማድረግ የምርጫ ሂደቱ እየተከናወነ ሲሆን ግንቦት 24 እለተ ሰኞ ከማለዳው ጀምሮ ድምፅ የሚሰጥ ይሆናል።
በዛሬው እለትም ባህርዳር ከተማ ምርጫ ክልል በሚገኙ 164 የምርጫ ጣቢያዎች ለድምፅ መስጫ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን የማሰራጨት ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
የምርጫ የቁሳቁስ ስርጭቱ በምርጫ ክልሉ ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የሚያገለግል ሲሆን የየምርጫ ጣቢያ ተወካዮችም የቀረቡላቸውን የምርጫ ቁሳቁሶች እየተረከቡ መሆኑ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሃይሉ፤ በትናንትናው እለት በሰጡት መግለጫ የቁሳቁስ ስርጭቱ ቀድሞ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
የቁሳቁስ ስርጭቱ በተያዘለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ሆኖ የምርጫ ጣቢያዎች ለምርጫው ዝግጁ እንደሚሆኑም አረጋግጠዋል።