ቀጥታ፡

በጂንካና አካባቢው ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ እየተሰራጨ ነው

ጂንካ፤ ግንቦት 22/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካና አካባቢው ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ የሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶች እየተሰራጩ ነው።

የፊታችን ሰኞ የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚፎካከሩበትና 54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 መራጮች የተመዘገቡበት ታሪካዊ የምርጫ ሂደት ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተሟላ ዝግጅት በማድረግ የምርጫ ሂደቱ እየተከናወነ ሲሆን ግንቦት 24 እለተ ሰኞ ከማለዳው ጀምሮ ድምፅ የሚሰጥ ይሆናል።

ለዚህም አስፈላጊ የሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶች በየምርጫ ጣቢያዎች ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል።

በዚሁ መሰረትም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካና አካባቢው የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭቱን በተመለከተ የኢዜአ ሪፖርተር ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

በጂንካና አካባቢው ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ የሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶች እየተሰራጩ መሆኑን ኢዜአ አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም