ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 22/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ናትናኤል ዳንኤል የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል።

ሀብታሙ ሸዋለም የኢትዮ ኤሌክትሪክን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በሊጉ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ45 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ46 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ድል አልቀናውም።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ናትናኤል ዳንኤል በሊጉ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ቁጥር 13 በማድረስ፣ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ደረጃ በ14 ጎሎች እየመራ ከሚገኘው የሲዳማ ቡናው አቤል ያለው በአንድ ግብ ብቻ ዝቅ ብሎ በሁለተኛነት ይከተላል።

በከባድ ዝናብ ምክንያት ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም የተቋረጠው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ፣ ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቆመበት ቀጥሎ ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም