ቀጥታ፡

በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ መቻልን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አሸናፊ ተገኝ እና ቴዎድሮስ በንቲ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ፈቱዲን ጀማል ለመቻል ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው አርባምንጭ ከተማ በ32 ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃ ይዟል።

ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት እያደረገ ባለው ትግል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። በሊጉም ስድስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል በ53 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ከሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማጥበብ እድል አልተጠቀመበትም። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ34ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 1፣ ሀዋሳ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም