ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተዘዋዋሪም ሆነ ተቀማጭ የዕጩ ወኪሎች ግዴታን በተመለከተ ባወጣው መረጃ

ማንኛውም ተዘዋዋሪም ሆነ ተቀማጭ የዕጩ ወኪሎች ግዴታ

1. የምርጫ ኃላፊው የሚሰጠውን ትዕዛዞች ማክበር አለበት፣

2. የምርጫ ሂደቱን ከሚያውኩ ተግባራት መቆጠብ አለበት፣

3. አግባብ ባለው አካል ሲጠየቅ መታወቂያውን ማሳየት አለበት፣

4. የምርጫ ሕጉን ማክበር አለበት፣

5. የምርጫውን ሂደት የመከታተል ተግባሩን ሲያከናውን መራጮች ማንን መምረጥ እንዳለባቸው አስተያየት ከመስጠት ወይም ተጽዕኖ ለማሳደር መሞከር የለበትም፣

6. የምርጫ ቁሳቁሶችን መያዝ፥ ማንሳት፤ መነካካት ወይም በቁሳቁሶቹ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ተግባራትን መፈጸም የለበትም፣

7. የምርጫ ጣቢያውን ኃላፊ ወይም ሠራተኛ ከማስፈራራት ወይም ሥራውን ከሚያደናቅፉ ተግባራት መቆጠብ አለበት፣

8. ወደ ድምፅ መስጫ ክፍሎች መግባት የለበትም፣

9. ቦርዱ የሚያወጣውን የሥነ ምግባር ደንብ መፈረም እና ማክበር ይገባዋል፡፡

ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 121

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም