ሉሲዎቹ ወደ ብሩንዲ አቀኑ - ኢዜአ አማርኛ
ሉሲዎቹ ወደ ብሩንዲ አቀኑ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ)፣ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታቸውን ከብሩንዲ አቻቸው ጋር ለማድረግ ወደ ስፍራው አቅንተዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ባደረገው ጨዋታ ብሩንዲን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ከጨዋታው መልስ ሉሲዎቹ የሀገር ቤት ዝግጅታቸውን ትናንት አጠናቀዋል።
በአሰልጣኝ ራውዳ አሊ የሚመራው ይኸው ስብስብ ረፋድ ላይ ወደ ቡጁምቡራ ማቅናቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የሁለቱ ሀገራት የመልስ ጨዋታ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓም በኢንትዋሪ ስታዲየም ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈች በመጨረሻው ዙር ማጣሪያ ከዛምቢያ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።