ቀጥታ፡

በጥሞና ወቅት ምን ምን ማድረግ አይቻልም?

ከዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ምርጫው ዕለት ድረስ ያሉት ቀናት የጥሞና ቀናት ናቸው።

በነዚህ ቀናት ውስጥ መከናወን የሌለባቸው ጉዳዮች ፦

👉በአካልና በዐደባባይ የሚደረጉ ቅስቀሳዎች ማካሔድ አይቻልም

👉ፖለቲካ ተኮር የሕዝብ ስብሰባዎችና ሠልፎች የቤት ለቤትና የዐደባባይ ላይ ቅስቀሳዎች አይካሔዱም ፤

👉የቅስቀሳ ኅትመቶችን እና ቁሳቁሶችን መለጠፍና ማሠራጨት እንዲሁም ለቅስቀሳ የሚያገለግሉ አልባሳትን መልበስም አይቻልም፤

በነዚህ የጥሞና ቀናት ውስጥም መገናኛ ብዙሃን ባሏቸው የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች፣ ፕላትፎርሞች ማስተናገድ የሌለባቸው ጉዳዮች ፦

👉በቀጥታ ሥርጭትም ሆነ የተቀረጹ የዕጩ ወይም የፓርቲ ፕሮግራሞችን ማስተላለፍ አይቻልም፤

👉እነዚህ ስርጭቶች የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾችን በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግንም የሚያካትቱ በመሆናቸው አይስተናገዱም፤

👉በየትኛውም አካባቢ የፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ ሥራዎች በነዚህ የጥሞና ቀናት አይስተናገዱም

የጥሞና ጊዜን ማክበር የምርጫውን ተዓማኒነት ያረጋግጣል! መራጩም ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወሥን ይረዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም