ቀጥታ፡

ለማላዊው የወዳጅነት ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/ 2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ አቻው ጋር ለሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

በዚህም መሠረት አቡበከር ኑራ፣ ፍሬው ጌታሁን እና ሰኢድ ሀብታሙ ጥሪ የተደረገላቸው ግብ ጠባቂዎች መሆናቸው ታውቋል።

በተከላካይ መስመር ደግሞ ፍቅሩ አለማየሁ፣ ጀሚል ያዕቆብ፣ ሳሙኤል ዮሐንስ፣ ፍጹም ፍትዓለው፣ ያሬድ ባየህ፣ ራምኬል ጀምስ፣ ርሆቦት ሰላሎ፣ ሬድዋን ሸሪፍ እና ግሩም ሀጎስ እንዲካተቱ ተደርጓል።

በአማካይ ክፍል ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾች ሀብታሙ ተከስተ፣ ሙሴ ከባላ፣ ቢንያም አይተን፣ ወገኔ ገዛኸኝ እና ቢንያም በላይ ናቸው።

በአጥቂ መስመር ደግሞ መስፍን ታፈሰ፣ አዲስ ግደይ፣ ቸርነት ጉግሳ፣ ፍፁም ጥላሁን፣ ቢንያም ፍቅሩ እና ዳዋ ሆጤሳ ተመርጠዋል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች የ34ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን ባከናወኑበት ማግስት ሪፖርት አድርገው ዝግጅት እንዲጀምሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥሪ አቅርቧል።

ፌዴሬሽኑ አክሎም የ34ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን መነሻ በማድረግ በተጫዋቾች ዝርዝር ላይ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎቹን ግንቦት 29 እና ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም