የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን ሊያደርግ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን ሊያደርግ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19 /2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ አቻው ጋር ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ያከናውናል።
ዋልያዎቹ ጨዋታዎቻቸውን የሚያደርጉት፣ የፊፋ ዓለም አቀፍ የብሔራዊ ቡድኖች የጨዋታ ቀናትን (FIFA Window) በመጠቀም መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ጨዋታዎቹ ግንቦት 29 እና ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም እንደሚከናወኑም አመልክቷል።