መጪው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም እያዘጋጀን እንገኛለን -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
መጪው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም እያዘጋጀን እንገኛለን -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የሕዝብ ጤናን እየጠበቅን፣ የነዋሪዎችን መተዳደሪያ አቅም እያጠናከርን መጪው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም እያዘጋጀን እንገኛለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ግዙፉ የቦረና የመጠጥ ውኃ አቅርቦትፕሮጀክት ለኅብረተሰቡ አስተማማኝ የንጹሕ ውኃ አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ፣ በምሥራቅ ቦረና እና በቦረና ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎችን ሕይወት እየቀየረ ይገኛል ብለዋል።
በብዙ ኪሎ ሜትሮች የሚቆጠሩ የቧንቧ መስመሮችን፣ ዘመናዊ የውኃ ማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና ሰፋፊ የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ያካተተ ዘላቂ መሠረተ ልማት እየገነባን ሲሆን ይህም ድርቅን ከመመከት የላቀ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት የሕዝብ ጤናን እየጠበቅን፣ የነዋሪዎችን መተዳደሪያ አቅም እያጠናከርን መጪው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም እያዘጋጀን እንገኛለን ብለዋል።