ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያን መረቁ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያን መረቁ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻ የሆነውን እና አዲሱን የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያን ዛሬ በይፋ መርቀዋል።
እንደ ቦይንግ 737 ማክስ ያሉ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ ዘመናዊ አውሮፕላን ማረፊያ፤ የአካባቢውን እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ልውውጥን እና ቱሪዝምን የማሳደግ ርዕይን ሰንቆ በሳምንት ሦስት በረራዎችን እንደሚያስተናግድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል፣ የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ሲሉም ገልጸዋል።
የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዳችን በእርግጥም`የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።