ቀጥታ፡

የላፍቶ ሆስፒታል ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2018 (ኢዜአ)፦ የላፍቶ ሆስፒታል ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ጽህፈት ቤቱ የላፍቶ ሆስፒታል በአዲስ አበባ ከተማ የጤና አገልግሎት ላይ የተጨመረ ትልቅ እመርታ እንደሆነ አመልክቷል።


 

የላፍቶ ሆስፒታል ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ገልጿል።

ሆስፒታሉ አዲስ አበባን የሕክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተቀመጠውን ሀገራዊ ግብ ከመደገፉም በላይ፣ ለሕክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለው ነው ያስታወቀው።

የተቋሙን አሁናዊ አቅምና ርዕይ በተመለከተ፤ በ5.4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ግዙፉ ሆስፒታል 17 ዘመናዊ ሕንጻዎችንና 500 አልጋዎችን ይዟል።

ተቋሙ የተገነባው የኢትዮጵያን የሕክምና አቅም ለማጠናከር፣ የላቁ የሕክምና አገልግሎቶች ተደራሽነትን ለማስፋት እና የልዩ ሕክምና መዳረሻ እንድትሆን የተጀመረውን ጥረት ለመደገፍ እንደሆነ ተገልጿል።


 

ሆስፒታሉ የላቀ የሕክምና ቴክኖሎጂን ያካተተ ሲሆን፤ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዘ የዲጂታል የቅድመ ካንሰር እና ድህረ ካንሰር የምርመራ ማሽን ጨምሮ የሚከተሉትን ዘመናዊ የሕክምና ቴክኖሎጂዎች አካቷል፦

👉ባለ 3-ቴስላ ኤም.አር.አይ (3-Tesla MRI) ማሽን፤

👉ባለ 640-ስላይስ ሲቲ ስካን (640-slice CT scan)፤

👉 በድምጽ የሚታዘዝ የካቴተራይዜሽን ላብራቶሪ (Cath Lab)፤

👉 የ3ዲ (3D) ማሞግራፊ መሣሪያ እና

👉የሮቦቲክስ ላብራቶሪ (TLA) መሣሪያ ናቸው።


 

እነዚህ ቴክኖሎጂዎች በሀገር ውስጥ ውስብስብ የሆኑ የጤና እክሎችን የመመርመር እና የማከም አቅምን በእጅጉ ያሻሽላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም