ሲዳማ ቡና ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና ለኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ መድንን በመለያ ምት አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መስፍን ታፈሰ እና ያሬድ ባየህ (በፍጹም ቅጣት ምት) የሲዳማ ቡና ግቦችን አስቆጥረዋል።
አማኑኤል ኤርቦ የኢትዮጵያ መድንን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል።
መደበኛው 90 ደቂቃ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት አምርቷል።
ሲዳማ ቡና በመለያ ምት 4 ለ 3 በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፏል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሪው ሲዳማ ቡና፣ በሁለት የውድድር መድረኮች ዋንጫ የማንሳት ግስጋሴውን ቀጥሏል።
የወቅቱ የሊጉ የዋንጫ ባለቤት ኢትዮጵያ መድን ዓመቱን በዋንጫ የማጠናቀቅ ህልም ሳይሳካ ቀርቷል።
ሲዳማ ቡና በፍጻሜው ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ይገናኛል።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ትናንት መቀሌ 70 እንደርታን በመለያ ምት ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ክለብ ኢትዮጵያን ወክሎ በቀጣዩ ዓመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።
የኢትዮጵያ ዋንጫ በ1937 ዓ.ም የተጀመረ አንጋፋ የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው።