ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂዷል - ኢዜአ አማርኛ
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የምረጡኝ ቅስቀሳ አካሂዷል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2018 (ኢዜአ)፦ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር አካሂዷል።
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ያካሄደ ሲሆን በቅስቀሳው የትብብሩ አመራሮች እና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፕሬዚዳንት አቶ አብረሃም ጌጡ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ምርጫው ሰላማዊ ትግልን ለማጠናከር እና ለማስቀጠል ዋነኛው መንገድ ነው።
ሰላማዊ ትግል ለሀገርና ለህዝብ ቀጣይነት የመጨረሻው ዋስትና መሆኑን መልዕክት አስተላልፈዋል።
የትብብሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አብረሃም ሃይማኖት በበኩላቸው፤ የትብብሩ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ የተጀመረውን ሰላማዊ ትግል ይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
ትብብር የሀገሪቱን ዘላቂ አንድነትና ልማት የሚያረጋግጡ ጠንካራ ፖሊሲዎችን በስፋት አዘጋጅቶ ወደ ምርጫው መግባቱንም አስገንዝበዋል።